About this app
ግዮን የአማራ ሕዝብ ዘላለማዊ ልሳን ነው፥ በዚሁ አምሳል የግዮን ድምፅም የሕዝባችን የዘመኑ ልሳን ሆና ታጭታለች ። የግዮን ድምፅ በነፃ መርሕ የተዋጀች፥ ከብሔረ አማራ ሕዝባችን በስተቀር ለማንም የማትወግን የአማራ ሕዝብ ድምፅ ናት። የግዮን ድምፅ የገናናው የብሔረ አማራ ዘላለማዊ ነፃ ሕዝብነት እና ልዑላዊ ማንነት ተምሳሌት ናት። የግዮን ድምፅ በአማራ ሕዝባችን ፖለቲካዊ፥ ኤኮኖሚያዊ፥ ማሕበራዊ እና ባሕላዊ አኗኗር እና ሁኔታ ዙርያ የሚያጠነጥን የተሟላ፥ የተረጋገጠ እና ያልተበረዘ መረጃ ለማቅረብ ትተጋለች። ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያን፥ የአፍሪቃ ቀንድንና እንዲሁም ዓለማችነን የሚመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችንም ታቀርባለች። የግዮን ድምፅ ዓቢይ ራዕይ በገዛ አገሩ ኢትዮጵያ በሰፈነው ጨቋኝ ፋሺስታዊ ስርዓት ወደር የሌለው ግፍ እና የመረጃ አፈና እየደረሰበት ላለውና ድምፁ ለታፈነው የአማራ ሕዝብ ድምፅ መሆን ነው። የግዮን ድምፅ በስደትም ሆነ በአገር ቤት የሚኖረውን መላውን ብሔረ አማራ ያለአንዳች የሃይማኖት፥ የፖለቲካ አመለካከት ወይም ሌላ የልዩነት ምክንያት በአንድ ግዮናዊነት ርዕዮት እና በአንድ ብሔረ አማራ ሕዝብነት ለማስተሳሰርና የኖረ የማይሻር አንድነቱን ለማበልፀግ ትተጋለች። የግዮን ድምፅ የቦርድ አባላት፥ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች የሰው ልጅ ነፃነትን እና ክብር የሚያስቀድሙ እሴቶችን ይጠነቅቃሉ፥ ያከብራሉ። የብሔረ አማራንም ሆነ የመላውን የሰው ልጅ በነፃ የማሰብ እና መረጃ የማግኘት ሰብዓዊ መብቶችንም ባላሰለሰ ታማኝነት ይጠብቃሉ። የግዮን ድምፅ መዳረሻ ግብ ጠንካራ፥ ምሉዕ እና የማይበገር አማራዊ ሃልዮት እና ማንነት ማስረፅ እና መገንባት ነው።
የግዮን ድምፅ ተልዕኮ በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙርያ የሚገኘውን ብሔረ አማራ የሚመለከቱ ነፃ፥ የተጣሩ እና ፋይዳ ያላቸው ዜናዎች እና ሌሎች መረጃዎችን ለሕዝባችን ማቅረብ ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን የከበረውን የብሔረ አማራ ጥንታዊ ቋንቋ፥ የተቀደሰ ባሕል ዕና ንዑድ ታሪክ የመንከባከብ፥ የማሳደግ እና የማበልፀግ ትውልዳዊ ሃላፊነታችነን እናስቀድማለን። መላው ተልዕኳችን እና ተግባራዊ እንቅሳቃሴያችን ዛሬ በገጠመው ፈተና ሕልውናው እና ማንነቱ አደጋ ላይ የወደቀው ብሔረ አማራ ሕዝባችን ሕልውናውን እና ታላቅ ሕዝብነቱን ለማረጋገጥ ከሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ጋር በፅኑዕ የተቆራኘ ነው።
የግዮን ድምፅ በዓለም ዙርያ ለሚገኘው ብሔረ አማራ ሕዝባችን አስተማማኝ እና በቀላሉ ተደራሽ የሆነ የመረጃ ምንጭ እንድትሆን ማስቻል ቀዳሚ ግባችን ነው። ጠቃሚ መረጃዎችን ብሎም ትምሕርታዊ፥ አዝናኝ፥አነሳሽ እና አጎልባች መርሐግብሮችን ለመላው ብሔረ አማራ ሕዝባችን ለማድረስ እንተጋለን። በአካባቢያዊ፥ ሐገራዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ደረጃ የተደራጁ ፥የተሰናዱ እና የተናበቡ ምሉዕ መረጃዎችን ለሕዝባችን ማድረስ፥ በዋናነት በግዮን ምድሩ የሚኖረውን ብሔረ አማራ ሕዝባችነን ማዕከል ያደረጉ እንደፍላጎቱ የተመጠኑ መርሐግብሮችን ማሰናዳት እና ተደራሽ ማድረግ የዘወትር ጥማታችን ነው። በተጨማሪም አሁን በኢትዮጵያ ባለው ሰው በላ የፋሺስት አገዛዝ በአማራ ሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና መከራ ብሎም በዚሁ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፌፀመ ያለውን ያልተለቀሰለት የዘር ማጥፋት ድርጊት (ጄኖሳይድ) ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ አበክረን እንሰራለን።
As Gihon is the Eternal Voice of the Amhara, Gihon Media Center is the Temporal Voice of our people. Gihon Media Center is an independent voice of the Amhara People. It represents the Eternal Free Spirit and Identity of our Amhara People. It strives to provide full, unadulterated and well-verified information about the political, economic, social and cultural life of the Amhara People. It also disseminates credible information about Ethiopia, the Horn of Africa and the World. Its main vision is to serve as the Voice of the Voiceless Amhara People that have been denied access to their own media outlets by the oppressive regime in Ethiopia. It seeks to unite all Amhara, at home and in the diaspora, irrespective of their religion, political opinion and other differentiating factors. The Board, Staff and volunteers of GMC are committed to the values of human freedom and dignity. They have an unwavering commitment to Freedom of Thought, Expression and Information. Their ultimate goal is to enhance a strong, comprehensive and thriving Amhara Consciousness and Identity.
App Permissions
Allows applications to access information about networks.
Allows applications to open network sockets.
Allows an app to create windows using the type TYPE_APPLICATION_OVERLAY, shown on top of all other apps.
Allows using PowerManager WakeLocks to keep processor from sleeping or screen from dimming.
Allows an application to manage access to documents, usually as part of a document picker.
Allows read only access to phone state, including the phone number of the device, current cellular network information, the status of any ongoing calls, and a list of any PhoneAccounts registered on the device.
Allows an app to use fingerprint hardware.
Allows access to the vibrator.
Allows an application to modify global audio settings.
Allows an app to access approximate location.
Allows an app to access precise location.
Required to be able to access the camera device.
Allows an application to read the user's contacts data.
Allows an application to read the user's calendar data.
Allows an application to write the user's calendar data.
Allows an application to read from external storage.
Allows an application to record audio.
Allows an application to write to external storage.
Allows an application to read or write the system settings.
Allows an application to read SMS messages.