About this app
መግቢያ
ይህ ፅሁፍ የተተረጎመው Diseases Treatment Dictionary ከሚለው የሞባይል አፕሊኬሽን ላይ ነው ። ይህንን አፕሊኬሽን Google play store ላይ ያገኙታል ።
ይህ አፕሊኬሽን ስለ ሰው ልጅ ዋና ዋና በሽታዎች Definition (የበሽታው ምንነት) , History (የበሽታው አመጣጥ ታሪክ), Epidemiology (በሽታው ያለባቸው ሀገሮች), Causes (የበሽታው መነሻ ምክንያት), Risk factors (ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች), Symptoms (የበሽታው ምልክቶች), Diagnosis and test (የበሽታው ምርመራ), Treatment and medications (ለበሽታው የሚሰጥ ህክምና) እና Prevention (በሽታው እንዳይዘን መከላከያ ዘዴ) ዝርዝር መረጃን ይሰጣል ።
ይህንን አፕሊኬሽን ለማዘጋጀት ያነሳሱኝ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የጤና አጠባበቅ ድጋፍ እና ትምህርት ስርጭት እጅግ በጣም አነስተኛ ነው ። የአካባቢን እና የራስን ንፅህና ከመጠበቅ ረገድ ፣ የተመጣጠነ ምግብ ከመመገብ ረገድ ፣ የህክምና ክትትል እና አዘውትሮ ሙሉ የጤና ምርመራ ከማድረግ ረገድ በአቅምም በተነሳሽነትም ረገድ እጅግ ብዙ ይቀረናል ። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ከ 90% በላይ ማህበረሰብ እነዚህ ክፍተቶች ይታዩበታል ። ነገር ግን ወደድንም ጠላንም ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች መተግበር ይኖርብናል ። ብዙ ጥራት ያላቸው የጤና ባለሙያዎች ያስፈልጉናል ። ብዙ ጤና ተቋሞች ያስፈልጉናል ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለሁሉም ማህበረሰብ የጤና አጠባበቅ ትምህርት መስጠት እጅግ ወሳኝ ነው ። በሽታን ተይዘን ከመታከም ይልቅ እንዳንያዝ መጣሩ እጅግ ጠቃሚ ፣ አዋጪ እና ዘላቂ መፍትሄ ነው ።
ስለዚህም የጤና አጠባበቅ ትምህርትን ለህብረተሰቡ ከማስተማር ረገድ ይህ አፕሊኬሽን ይጠቅማል ። በአሁኑ ወቅት በከተማ ያለው አብዛኛው ማህበረሰብ የ smart ሞባይል ስልኮች ባለቤት ነው ። ስለዚህ ይህን አፕሊኬሽን ያለምንም ወጪ በስልኩ ላይ መጠቀም ይችላል ። ነገርግን ለገጠር ነዋሪው ህዝብ ተደራሽነቱ ጥቂት ነው የሚሆነው ።
በተጨማሪም ይህ አፕሊኬሽን የጤና ሙያ ለመማር ለሚፈልጉ ሰዎች ጥሩ ማነሳሻ ይሆናል ብዬ አምናለው ።
በተጨማሪም ሁላችንም ስለ ሰውነታችን አሰራር እና ሰውነታችንን ስለሚያጠቁት በሽታዎች ማወቃችን ለአለማዊዉም ሆነ ለመንፈሳዊ ህይወታችን እውቀት ይሰጠናል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የባህላዊ ህክምና በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል ። ነገርግን አብዛኞቹ ተጠቃሚዎችም ሆኑ ባህላዊ ሃኪሞች የሰው ልጅ ጤናን በተመለከተ ብዙም ሳይንሳዊ እውቀቱ የላቸውም ። ስለዚህ ይህ አፕሊኬሽን ይህንን ክፍተት በተወሰነ ረገድ ይሞላል ።
በዚህ ዘመን ወረርሽኝ እየተከሰቱ ናቸው (ለምሳሌ ኮሮና በሽታ) ። ወረርሽኝ ደግሞ የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበረሰባዊ አቋም በጣም ይጎዳል ። ነገርግን ስለ ሰውነታችን አሰራር ፣ ስለ በሽታዎች እና ስለ ጤና አጠባበቅ እውቀት ብናዳብር እነዚህን ወረርሽኝ እንዳይከሰቱ ፣ ከተከሰቱም ኢኮኖሚያዊ እና ማህበረሰባዊ ጉዳት ሳይደርሱ መከላከል እንችላለን ማለት ነው ።
ወዳጆቼ ይህ የትርጉም ስራ ለከተሜው ወይንም የተሻለ ሳይንሳዊ እውቀት ላለው ሰው ደረጃውን ያልጠበቀ ትርጉም ሊሆን ይችላል ። ነገርግን ገጠር ላሉት እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን በጣም ጠቃሚ ነገር ሊሆን ይችላል ። በመጀመሪያ ገጠር ያሉ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን አብዛኞቹ ትምህርት ቤት አይሄዱም ፣ ሁለተኛ ትምህርት ቤት የሚሄዱት ጥራት ያለው ትምህርት አያገኙም ፣ ሶስተኛ በቤት ውስጥ ስራ ብዙ ጫና አለባቸው ። ስለዚህ ይህ የትርጉም መፅሀፍ ለእነዚህ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን በተወሰነ ረገድ ይጠቅማል ። ነገርግን ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ከባድ ነው ። ወደፊት በድምፅ ፣ በቪዲዮ እና በመፅሀፍ ቢዘጋጅ መልካም ይመስለኛል ። መንግስት በገጠራማው አካባቢ ትምህርት እንዲስፋፋ ማድረግ ይኖርበታል ። እኛም በቻልነው አቅም ገጠር ላሉት እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን ትምህርታዊ ድጋፍ ማድረግ አለብን ።
በቅርብ ጊዜ ያነበብኩት የነጋድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ "መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር " የሚለው መፅሀፍ እጅግ ካስደነቁኝ መፅሀፎች ውስጥ አንዱ ነው ። እሳቸው ይህንን ጥልቅ የሆነ ሃሳብ በቀላል አማርኛ ሲገልጡት በጣም ገረመኝ ። በተጨማሪም የአንድ ሃገር እድገት በህዝቦቹ እውቀት ላይ ይመረኮዛል የሚለው አስተሳሰባቸው በጣም ስላሳመነኝ እኔም ይህ መፅሀፍ የአገሬን ህዝብ እውቀት ሊያሳድግ ይችላል ብዬ በማመን ለመተርጎም አሰብሁ ።
ነገርግን ይህ መፅሀፍ 2 ትላልቅ ችግሮች አሉበት ። እነዚህም
1 በግርድፍ አማርኛ መቅረቡ ።
2 ጥልቅ የሆነ ትንተና አለመስጠቱ ።
የዚህ አፕሊኬሽን ይዘት የሚከተሉት ናቸው ።
በባክቴሪያዎች የሚመጡ በሽታዎች
ይህንን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲጠቀሙ ጥሩ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ። ከዚያ በሃላ ያለ ኢንተርኔት ኮኔክሽን መጠቀም ትችላላችሁ ። የመወያያ ገፁን ለመጠቀም ግን ኢንተርኔት ኮኔክሽን ያስፈልጋል ።
ይህ አፕሊኬሽን update ሳያስፈልገው ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ስለሚያስችል ከግዜ ወደ ግዜ አዳዲስ የተጨመሩ ነገሮች ሊኖሩት ስለሚችል በየተወሰነ ቀናት ኢንተርኔት ኮኔክሽን ከፍተን ከዚያ አፕሊኬሽኑን መክፈት ይመከራል ። ለምሳሌ የተጨመረ ክፍል ካለ ኢንተርኔት ከፍታችሁ ይህን የተጨመረውን ክፍል አፕሊኬሽኑ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ ።
ይህንን አፕሊኬሽን ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍቱ ስሞትን ማስገባት አለቦት ።
ይህንን መፅሃፍ ስናነብ ስለ ሰውነታችን አሰራር እያነበብን ቢሆን የበለጠ ይገባናል ። ስለዚህ Google play store ላይ እኔ ያዘጋጀሁት "የሰውነታችን አሰራር" የሚል አፕሊኬሽን ስላለ ይህንን አፕሊኬሽን ስልካችሁ ላይ ጭናችሁ ከዚህኛው አፕሊኬሽን ጋር ጎን ለጎን ብታነቡት የተሻለ ይመስለኛል ።
ይህ አፕሊኬሽን የመወያያ ገፅ አለው ።
ይህ አፕሊኬሽን ለእናቴ ለ ወ/ሮ አታለለች ገ/የሱስ መታሰቢያ ይሁንልኝ ። እማዬ የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ነፍስሽን በገነት ያኑረው ።
መልካም ንባብ
ከ አብርሃም ገበየሁ
App Permissions
Allows an application to write to external storage.
Allows applications to open network sockets.
Allows applications to access information about networks.
Allows using PowerManager WakeLocks to keep processor from sleeping or screen from dimming.
Allows applications to access information about Wi-Fi networks.
Allows an application to receive the ACTION_BOOT_COMPLETED that is broadcast after the system finishes booting.
Allows an application to read from external storage.